Calling all job seekers, employers, recruiters and community partners! Help shape the future of the WorkSourceWA website. Join the website study (Part 2) for a chance to win a $100 Visa e-gift card!
English | Español
በዚህ ገጽ ላይ
የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች | ተከፋይ ቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ | ስራዎች እና ስልጠና
የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች
በ 800-410-0758 በመደወል ያመልክቱ። በአማርኛ እርዳታ ለማግኘት ኤክስቴንሽን 14 ይደውሉ (ተርጓሚዎች በነጻ ይገኛሉ)። መስማት የተሳናቸው፣ መስማት የማይችሉ፣ ወይም መናገር የማይችሉ በ 711 ላይ ለዋሽንግተን ሪሌይ አገልግሎት(Washington Relay Service) ይደውሉ።
ቁጥሩን ሲደውሉ፣ በእንግሊዝኛ ይህንን መልእክት (wav ፋይል) ሊሰሙ ይችላሉ። እንዲህ ይላል:
"በጥሪዎች ብዛት ምክንያት ፣ በዚህ ሰዓት ጥሪዎን መቀበል አንችልም። እባክዎን በኋላ መልሰው ይደውሉ፣ ወይም የሥራ አጥነት መረጃን በዌብሳይታችን www.esd.wa.gov ላይ ይግኙ። ስለ ትግስትዎ እናመሰግናለን። ደህና ይሁኑ።"
የቱንም ያክል ከፍተኛ የጥሪ መጠን ቢኖርም እርስዎን ለመርዳት ቁርጠኞች ነን። የቋንቋ አስተርጓሚዎች አሉን። በስልክ ማመልከት ከፈለጉ እነዚህ ምክሮች ሊረዱዎት ይችላሉ።
- አስቀድመው ወይም ወደ ኋላ ላይ ይደውሉኦፕሬተርን የማግኘት እድሎችዎን ይጨምሩ።
የይገባኛል ጥያቄዎች ማእከል ሰዓቶች እና መረጃ። - ስልኩን ይመልሱ። እኛ ልንሆን እንችላለን! ስማችን በእርስዎ የደዋይ መታወቂያ ላይ አይታይም። ጥሪያችንን ካጡ፣ መልሰው ሊደውሉልን ይገባል፣ ይህም በማመልከቻ ሂደትዎ ላይ ተጨማሪ ጊዜ ይጨምራል።
ማመልከቻ:-
- በበይነ መረብ ስለ ስራ አጥነት ሲያመለክቱ ስለምንጠይቅዎ ነገር የበለጠ ይረዱ።
- የዩኤስ ዜጋ ካልሆኑ አሁንም ለስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ማመልከት ይችላሉ። ስለ ዜግነት እና የመስራት ህጋዊ መብትዎ የበለጠ ይወቁ።
ክፍያ ያለው የቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ (Paid Family & Medical Leave)
ክፍያ ያለው የቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ (Paid Family & Medical Leave) ለዋሽንግተን ሰራተኞች የሚሰጥ ጥቅም ነው። ከባድ የጤና እክሎች እንዳይሰሩ ሲከለክልዎት ወይም የቤተሰብ አባልን ለመንከባከብ ጊዜ ሲፈልጉ፣ ከአዲስ ልጅ ጋር ግንኙነት ሲፈጥሩ ወይም በውጭ አገር ለውትድርና አገልግሎት ከሚዘጋጅ የቤተሰብ አባል ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እዚህ አለልዎት።
ክፍያ ስላለው ፈቃድ (Paid Leave) የበለጠ ይረዱ።
ስራዎች እና ስልጠና (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ)
WorkSource ቀጣዩን ተግባርዎን ወይም ስራዎን እንዲያገኙ ይረዳዎታል። ለመጀመር ወደ WorkSourceWA.com ይሂዱ። በሪሶርስስ (Resources) ስር፣ በአቅራቢያዎ የሚገኝ ቢሮ ለማግኘት እና ምን አይነት አገልግሎቶች በቨርቹዋል እና በአካል እንደሚገኙ ለማየት የWorkSource locator (የሥራ ምንጭ ጠቋሚ) አመልካች ይጠቀሙ።