ለስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች እንዴት ማመልከት ይችላሉ

የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች በእርስዎ ጥፋት ባልሆነ ምክንያት ስራዎን ሲያጡ ጊዜያዊ ገቢ ያስገኙልዎታል። ገንዘቡ እርስዎ ያጡትን የተወሰነ ገቢ የሚተካልዎ ሲሆን፣ አዲስ ስራ እስከሚይዙ ድረስም ወጪዎችን ለመሸፈን ያግዝዎታል። ጥቅማ ጥቅሞቹ የሚገኙት የቀድሞ አሰሪዎ(ዎችዎ) ከከፈሉት ግብር ነው። ጥቅማ ጥቅሞቹ በገንዘብ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አይደሉም— ስራዎን ያጡት በቅርቡ በመሆኑ ወይም ባለመሆኑ ላይ ብቻ እንጂ።

ከመጀመርዎ በፊት፣  አሁን የተለመዱ ጥያቄዎች የሚሰጡ ምለሶችን ይመልከቱ።


በቀጥታ መስመር ላይ ያመልክቱ (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ ብቻ)

የተሻለውና ፈጣኑ የማመልከቻ መንገድ በቀጥታ መስመር ላይ ነው። የቀጥታ መስመር ማመልከቻው የሚገኘው በእንግሊዝኛና ስፓኒሽ ብቻ ነው። ከማመልከትዎ በፊት፣ ብቁ መሆንዎን ያጣሩ እና ለማመልከት ምን እንደሚያስፈልግዎም ይወቁ፡

  • ጥቅማ ጥቅሞች የሚቀርቡት በ COVID-19 ምክንያት ስራቸውን ያጡ ሰዎችን ለማገዝ ነው። ብቁ መሆንዎትን እዚህ ላይ ያጣሩ።
  • ለመደበኛ የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች ብቁ መሆንዎን ለማወቅ ይህንን ዝርዝር ይመልከቱ።
  • ለመደበኛ የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅም ከማመልከትዎ በፊት፣ ይህንን ቼክሊስት በማውረድ  ለመዘጋጀት ይታገዙ።
  • በግል ስራ የሚተዳደሩ ከሆኑ ወይም በ COVID-19 ምክንያት ስራዎትን ካጡና ለመደበኛ የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች ብቁ ካልሆኑ፣ ለዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የስራ አጥነት ድጋፍ (Pandemic Unemployment Assistance) ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ከማመልከትዎ በፊት (በቅድሚያ ለመደበኛ ስራ አጥነት ማመልከት አለብዎት)፣ ይህንን ቼክሊስት  ያውርዱ።


አሁን በቀጥታ መስመር ላይ ያመልክቱ

(እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ ብቻ)


በስልክ ያመልክቱ (አስተርጓሚዎች አሉ)

በስልክ ማመልከት ይችላሉ። በርካታ ሰዎች በ COVID-19 አለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት የክፍያ ጥያቄዎቻቸውን በተመለከተ ስልክ ስለሚደውሉ የጥሪ ቆይታ ጊዜያት በአሁኑ ጊዜ በጣም ረዥም ናቸው። እርስዎን ለማገዝና የቋንቋ አስተርጓሚዎችን ዝግጁ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን፤ ስለዚህ በስልክ ለማመልከት ከፈለጉ፣ እነዚህ ጠቃሚ መረጃዎች ሊያግዙ ይችላሉ።

አስቀድመው ወይም ዘግይተው ይደውሉ
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት ውስጥ ከ 7 a.m. እስከ 4 p.m. ድረስ የስልክ ጥሪዎችን እንቀበላለን። አስቀድሞ ወይም አዘግይቶ መደወል ወደ ኦፕሬተር የመድረስ ዕድልዎን ይጨምረዋል።

ስልክዎን ያንሱ
ደዋዮቹ እኛ ልንሆን እንችላለን! ስማችን በደዋዩ መለያ ስም ላይ አይታይም። ስልካችንን ሳያነሱ ከቀሩ፣ መልሰው ሊደውሉልን ይገባል፤ ይህ ደግሞ የማመልከቻ ሒደትዎ ላይ ተጨማሪ ጊዜን የሚያስከትል ነው። 

በስልክ ለማመልከት፣ በዚህ ቁጥር ይደውሉ 800-318-6022።